ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ|ደሴ ከተማ ከፌደራል ፖሊስ

image

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በበዓል ዋዜማ ምክንያት ከእሁድ ወደ ነገ የተዛወሩ ሲሆን ነገ ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ደሴ ላይ ደሴ ከተማ ከፌደራል ፖሊስ የሚያደርጉትን ጨዋታ በቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ አምዳችን ተመልክተነዋል ። ወደ ላይኛው የኢትዮጵያ ሊግ ወደሆነው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ አንደኛ ሆኖ ማጠናቀቅ መስፈርት በሆነበት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ገና ከተጀመረ 5ሳምንታትን ያስቆጠረ ሲሆን በርካታ ፉክክር እየታየበት ይገኛል።በዚህ ምድብ ከሚገኙ ክለቦች አንዱ የሆነው ደሴ ከተማ ነገ ሶስተኛ የሜዳ ላይ ጨዋታውን የሚያደርግ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥሩ መሻሻል እያሳየ ጥሩ ጨዋታ ለተመልካች ቢያስመለክትም ከሜዳ ውጭ ያለውን መጥፎ አጀማመር ማስተካከል ተስኖታል ።ከሜዳ በወጣባቸው 3 ጨዋታዎች 6ጎሎች ተቆጥረውበት 3 ጎል አስቆጥሮ ማግኘት ከነበረበት 9 ነጥብ አንድ እንኳ ይዞ አለመመለሱ ባለፈው ዓመት ያጣውን ወደ ፕሪሚየር ሊግ የማደግ ዕድል ለማሳካት የሚያደርገውን ጉዞ ገና ከጅምሩ ጥያቄ ውስጥ የከተተው ሲሆን በተለይም ጨዋታዎች በተጀመሩ በመጀመሪያዎቹ 10-15 ደቂቃ ጎል ማስተናገዱ የበለጠ ተጫዋቾች በውጥረት እንድጫወቱ በር ይከፍታል ።በተለይ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ቢሾፍቱ ላይ ገላንን በገጠመበት ጨዋታ ገና በሶስተኛው ደቂቃ ጎል ማስተናገዱን ተከትሎ ደሴዎች የአቻነት ጎል ፍለጋ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም ልፋታቸው ፍሬ ሳያፈራ ቀርቷል። ባለፉት አመታት በሜዳው ብዙ ሽንፈቶችን ሲያስተናግድ የነበረው ደሴ ዘንድሮ በሜዳው ጥሩ አጀማመር ያሳየ ሲሆን ከሜዳ ውጭ ባለው መጥፎ አጀማመር በደጋፊዎች ከፍተኛ ትችት እያስተናገዱ የሚገኙት አሰልጣኝ አረጋይ ወንድሙ ባለፈው ሳምንት ያጡትን ነጥብ ለማግኘት እና በደጋፊ ፊት ያለውን ጥሩ አጀማመር ለማስቀጠል ለነገው ጨዋታ ሙሉ ሶስት ነጥብ ለማግኘት ቡድናቸውን እየመሩ ወደ ሜዳ ይገባሉ።ከባለፉት አመታት በተለየ መልኩ በርካታ ደጋፊዎች በጨዋታው መታደማቸው ለክለቡ ጥሩ መነቃቃት የፈጠረለት ይመስላል ።በ5ኛ ሳምንት ለቡድኑ ግልጋሎት ያልሰጡ በርካታ ተጫዋቾች ለነገው ጨዋታ መመለሳቸው ለቡድኑ መልካም ዜና ነው። ተጋባዡ ፌደራል ፖሊስ ባንፃሩ እስካሁን ካደረጋቸው 5 ጨዋታዎች በአንዱ አሸንፎ በ 3 አቻ እና አንድ ጊዜ ተሸንፏል ።ባለሜዳው ደሴ 3 አሸንፎ ሶስት ተሸንፏል ።የጎል ብዛት ስንመለከት ደሴ 6 አስቆጥሮ 6 የተቆጠረበት ሲሆን ፌደራል ፖሊስ 2 አስቆጥሮ 2 ተቆጥሮበታል። ይህም የሚያሳየን ፌደራል ፖሊስ ጥሩ የመከላከል አቅም ሲኖረው በአንፃሩ ደሴ በማጥቃት በኩል የተሻለ መሆኑን ነው። ይህም ለደሴ ነገ የደሴ አጥቂዎች በፌደራል ፖሊስ ተከላካዮች ከባድ ፈተና ይጠብቃቸዋል ተብሎ ይገመታል ።ፌደራል ፖሊስ እስካሁን ከሜዳ ውጭ ከወጣባቸው 3 ጨዋታዎች አንዱን አሸንፎ (ወልዲያን) አንዱን ተሸንፎ (ኮምቦልቻ ) ቀሪውን አቻ ወጥቶ አጠናቋል። 2 ጎልም አስቆጥሮ የተቆጠረበት ከሜዳው ውጭ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ነበር። ሁለቱም ቡድኖች እኩል 6 ነጥብ ይዘው በደረጃ ሰንጠረዡ 6ኛ እና 8ኛ ደረጃ የሚገኙ ሲሆን ከመሪው ለገጣፎ ያላቸውን የ6 ነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ይፋለማሉ ። በደሴ በኩል ሁሉም ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ።
የእርስ በርስ ግንኙነቶች
-እስካሁን በሊጉ አራት ጊዜ ተገናኝተው ደሴ ሶስት ጊዜ ፌደራል ፖሊስ አንድ ጊዜ በተመሳሳይ 1-0 አሸንፈዋል ።
– ደሴ ላይ ሁለት ጊዜ ተገናኝተው ደሴ ሁለቱንም 1-0 አሸንፏል ።
-በድምሩ 4 ጎሎች ተቆጥረዋል ።
ግምታዊ አሰላለፍ
ደሴ ከተማ(4-3-3)
ከፍያለው አንጀባው
አንዋር ሙሀመድ -አቤል አበበ-ማታይ ሎል-አንሷር ሙሀመድ
አሸናፊ ከበደ-ተስላች ሳይመን-ከፍያለው ወለላው
ተካልኝ መስፍን -አክዌር ቻም-በድሩ ኑርሁሴን

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started