15 (አርብ) መቐለ ላይ ደደቢት ከገላን ያደረጉት ጨዋታ በባለሜዳዎቹ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። የደደቢትን ሁለቱንም የድል ጎሎች ማስቆጠር የቻለው ክብሮም አስመላሽ ነው።
አዲስ አበባ መድን ሜዳ ላይ አቃቂ ቃሊቲ የምድቡን መሪ ለገጣፎ ለገዳዲን አስተናግዶ 2-1 ሽንፈት አጋጥሞታል። የገጣፎ ለገዳዲን የድል ጎሎች አንዋር ያሲን እና ዘካሪያስ ከበደ ሲያስቆጥሩ ለአቃቂ ከመሸነፍ ያላዳናቸውን ግብ አብዱልቃድር ናስር አስቆጥሯል።
በምድቡ ዛሬ የተደረጉት ሌሎች ጠዋታዎች ማለትም ፌዴራል ፖሊስ ከ ሰሎዳ ዓድዋ፣ ወልዲያ ከ ደሴ ከተማ እንዲሁም ኤሌክትሪክ ከሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ያለ ግብ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ ወሎ ኮምበልቻ ከ አክሱም ከተማ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በትራንስፖርት ችግር ምክንያት ሳይከናወን ቀርቷል።

